የኢራን ጦር ተጨማሪ ሁለት ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዦቹ መገደላቸውን አስታወቀ

ሟቾቹ የጠቅላይ ኢታማዦር የስለላ ምክትል ኃላፊ ጎላምሬዛ መህራቢ እና የአሠራር ክፍል ምክትል ኃላፊ መህዲ ራባኒ ናቸው።

እስራኤል በኢራን በፈጸመችው ጥቃት የኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ዘብ ዋና አዛዥ፣ የአገሪቱ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም እንዲሁም ስድስት የኒውክሌር ሳይንቲስቶች መገደላቸውን የኢራን መንግሥታዊ ሚዲያ ዘግቧል።

እስራኤል በፈጸመችው ጥቃት 78 ሰዎች መገደላቸውን እንዲሁም 320 ኢራናውያን መቁሰላቸውን ያስታወቀችው ኢራን አብዛኞቹ ሰላማውያን ዜጎች ናቸው ብላለች።

እስራኤል የፈጸመችውን ጥቃቶች “አረመኔያዊ” እንዲሁም “ወንጀል” ነው ሲሉ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የኢራን ተወካይ ሰኢድ ራቫኒ ተናግረዋል።

የእስራኤል ጥቃትን ተከትሎ ኢራን ባቀረበችው ጥያቄ በኒውዮርክ ለተሰበሰበው የተባበሩት መንግሥታት የጸጥታው ድርጅት ነው ተወካዩ ይህንን የተናገሩት።

ሰኔ 7 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *