የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር አገልግሎት 104 ባለ 20 ጫማ ከፍታ ያላቸው ኮንቴነሮች ማቅረቡን አስታወቀ

እቃ መጫኛዎቹን ከሜዲትራኒያን የባሕር ትራንስፖርት ኩባንያ ጋር በመተባበር ከጅቡቲ ወደብ ወደ እንዶዴ ባቡር ጣቢያ ማጓጓዙን አስታውቋል፡፡

ኮንቴነሮቹ ከፍተኛ ጥራት ያለው ቡና፣ እህል እና ሌሎች ለውጭ ገበያ ለሚቀርቡ ምርቶች የሚያገለግሉ ሲሆን የሀገር ውስጥ አምራቾች እና ላኪዎች ምርት ለዓለም አቀፍ ገበያ እንዲደርስ በማድረግ የኢትዮጵያን የውጭ ገበያ ኢኮኖሚ ይደግፋሉ ተብሏል።

በተጨማሪም ላኪዎች በጅቡቲ ወደብ የኮንቴነር አገልግሎት ለማግኘት የሚባክንባቸውን ጊዜና ወጪ ያስቀራል ሲል የኢትዮ ጅቡቲ ባቡር አክሲዮን ማህበር አስታውቋል።

ሰኔ 10 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *