የሀረሪ ክልል ጤና ቢሮ የበልግ ዝናብን ተከትሎ የወባ ስርጭት ጭማሪ ማሳየቱን አስታዉቋል፡፡
ከኢትዮ ኤፍኤም ጋር ቆይታ ያደረጉት በክልሉ ጤና ቢሮ አስተባባሪ አቶ አብዲ አሊዬ፤ ክልሉ ወይናደጋ በመሆኑ ህብረተሰቡ ለወባ ስርጭት ተጋላጭ መሆኑን ተናግረዋል።
የወባ ስርጭቱ ያለባቸዉ ቦታዎች እንደ ከተማ በስድስት ወረዳ መከፈላቸዉን ገልጸዋል፡፡
በአብዛኛዉ እንዲህ አይነት ኬዞች የሚመጡት ከኤረር ወልድያ የሚባል ቀበሌ መሆኑን አንስተዉ፤ ሀረር ከተማ ዉስጥም አልፎ አልፎ ችግሩ እንደሚታይ ተናግረዋል፡፡
የባለፈዉ አመት የበልግ ዝናብን ተከትሎ እንደ ሀገር የወባ በሽታ ስርጭት መጨመሩን የሚገልጹት አቶ አብዲ፤ እንደ ክልልም ላለፉት አምስት፣ ስድስት አመታት ያልተመዘገቡ የወባ ኬዞች እንደነበሩ አንስተዋል።
ጥቅምትና ህዳር አካባቢ የመቀነስ አዝማሚያ ነበረዉ ያሉን አቶ አብዲ፤ በአሁን ወቅት እየጨመረ መምጣቱን ገልጸዋል፡፡
በተመላላሽ ህክምና ሲደረግላቸዉ መቆየቱን ገልጸዉ፤ ምንም አይነት ሞት አለመመዝገቡን ነግረዉናል፡፡
ሊዲያ ደሳለኝ
ሰኔ 13 ቀን 2017 ዓ.ም
