የአሜሪካ ጥቃት የኢራን ኒውክሌር ይዞታዎችን እንዳላወደመ የደህንነት ግምገማ አሳየ

አሜሪካ በኢራን ላይ የፈጸመችው ጥቃት የኒውክሌር ማብላያ ይዞታዎችን እንዳላወደመ የአሜሪካ መከላከያ ማዕከል (ፔንታጎን) የደህንነት ግምገማ አሳየ።

ቅድመ ግምገማው ጥቃቱ የኢራንን የኒውክሌር መርሃ ግብር ምናልባትም በወራት ወደኋላ ሊመልሰው እንደሚችል ነው ያሳየው።

ኢራን ያበለጸገችው የዩራኒየም ክምችት አሜሪካ ቅዳሜ፣ ሰኔ 14/ 2017 ዓ፣ም በፈጸመችው ጥቃት አለመውደሙን የአገሪቱ የመከላከያ ደህንነት ኤጀንሲ ግምገማን የሚያውቁ ምንጮች ለቢቢሲ የአሜሪካ አጋር ሲቢኤስ ተናግረዋል።

ዋይት ሃውስ በበኩሉ “ይህ ፍጹም የተሳሳተ” ግምገማ” በማይረባ የደህንንት ማህበረሰብ ሾልኮ የወጣ ነው” ሲል ውድቅ አድርጎታል።

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በበኩላቸው የኢራን የኒውክሌር ይዞታዎች ሙሉ በሙሉ ወድመዋል በማለት በድጋሚ አጽንኦት ሰጥተው፤ “በታሪክ ውስጥ ስኬታማ ከሆኑ ወታደራዊ ጥቃቶች መካከል አንዱ የሆነውን ለማዋረድ” በሚዲያዎች የሚደረግ ሙከራ ሲሉ ከሰዋል።

ሰኔ 18 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *