በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል 1 መቶ 80 ሰዎች በትራፊክ አደጋ ህይወታቸዉ አልፏል ተባለ፡፡

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጀት አመቱ በደረሰ የትራፊክ አደጋ 1 መቶ 80 ሰዎች በመኪና አደጋ ህይወታቸዉ ማለፉን የክልሉ የትራፊክ አደጋ መከላከልና ቁጥጥር አስታዉቋል፡፡

የክልሉ የትራፊክ አደጋ መከላከልና ቁጥጥር ዳይሬክተር ምክትል ኮማንደር ታረቀኝ ከበደ፤ በክልሉ በሚገኙ ሰባት ዞኖችና ሶስት ልዩ ወረዳዎች በበጀት አመቱ 2 መቶ 31 የትራፊክ አደጋዎች ደርሰዋል ብለዋል።

በዚህ በደረሰዉ 231 የትራፊክ አደጋ የ180 ዜጎችን ህይወት ሲቀጥፍ፤197 ሰዎች ላይ ከባድ፤በ76 ሰዎች ላይ ቀላል የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል ሲሉ ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።

በጠቅላላዉ በአደጋዉ ሰለባ ከሆኑ 453 ተጎጂዎች ዉስጥ 3 መቶ 33ቱ ወንዶች ሲሆኑ 1መቶ20 ሴቶች መሆናቸዉ ኃላፊዉ ተናግረዋል።

በአደጋዉ 28 ሚሊዮን 623 ሺህ ብር የሚገመት ንብረት መዉደሙንም ተናግረዋል፡፡

በ2016 በጀት ዓመት 234 የትራፊክ አደጋ ተመዝግቦ እንደነበር የተናገሩት ምክትል ኮማንደር ታረቀኝ፤በዘንድሮዉ አደጋዉን በአስር በመቶ ለመቀነስ ታቅዶ ወደ ተግባር ቢገባም መቀነስ የተቻለዉ ግን 2 በመቶ ነዉ ብለዋል፡፡

ልኡል ወልዴ

ሰኔ 24 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *