ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ዛሬ በኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው ከምክር ቤት አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽ እየሰጡ ነው።
ቀሪ ከ4 ሚሊየን ያነሱ ተረጂዎችን በአጭር ጊዜ ዉስጥ መሰል ተግባራትን በመፈፀም ከተረጂነት ነጻ ይወጣሉ ብለዋል፡፡
ኢትዮጵያ በአጭር ጊዜ ዉስጥ ከምግብ ተረጂነት በማላቀቅ የምግብ ሉዓላዊነቷ የተረጋገጠ ሀገር መሆኗን እናሳየለን ነዉ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ።
ባለፈዉ ዓመት 26 ሚሊየን ሄክታር መሬት ማረስ ተችሏል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ በዚህኛዉ ዓመት 5.8 ተጨማሪ ቦታ በማረስ 31.8 ሄክታር መሬት ማረስ ተችሏል ብለዋል፡፡
ባለፈዉ ዓመት በሁሉም ምርት በጥቅሉ 1.2 ቢሊየን ኩንታል ምርት መሰብሰብ መቻሉን ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ዘንድሮ 3 ሚሊየን ኩንታል ጭማሪ በማሳየት 1.5 ቢሊየን ኩንታል ምርት መሰብሰብ መቻሉን ገልጸዋል፡፡
ሊዲያ ደሳለኝ
ሰኔ 26 ቀን 2017 ዓ.ም
