ሩስያ አፍጋኒስታንን ለሚያስተዳድረው መንግሥት ዕውቅና በመሰጠት የመጀመሪያዋ አገር ልትሆን ነው።
ውሳኔውን የአፍጋኒስታኑ ውጪ ጉዳይ ሚኒስትር አሚር ካሃን ሙታኪ “ወኔ የተላበሰ” ሲሉ አሞካሽተውታል።
ሚኒስትሩ በአፍጋኒስታን የሩሲያ አምባሳደር ከሆኑትን ዲሚትሪ ዝሃሮኖፍን በካቡል ትናንት ሐሙስ ተገናኝተዋል።
በዚህ ወቅት የሩስያው አምባሳደር የአገራቸውን ውሳኔ ለአፍጋኒስታን መንግሥት አሳውቀዋል።
ሙታኪ ውይይታቸው “አዲስ አዎንታዊ ግንኙነት፣ የእርስ በእርስ መከባበርን እና ገንቢ ተሳትፎ የታየበት” ነበር ብለዋል።
አክለውም ውሳኔው ለሌሎች አገራት ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ ገለጸዋል።
በአፍጋኒስታን የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት ተበርክቷል የሚሉ ሪፖርቶች በስፋት ቢደመጥም በአውሮፓውያኑ 2021 ዳግም ሥልጣን የተቆጣጠረው ታሊባን ዓለም አቀፍ እውቅናን እና ኢንቨስትመንትን ከሌሎች አገራት ሲጠይቅ ቆይቷል።
የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ታሊባን ሽብርተኝነትን ለመዋጋት “አጋር” ነው በማለት ባለፈው ዓመት ሐምሌ ወር ላይ ተናግረዋል።
በአውሮፓውኑ 1979 ሶቪየት ኅብረት አፍጋኒስታንን ከወረረች እና ለ9 ዓመታት ተዋግተው በሁለቱም ወገን በኩል በደምሩ 15 ሺህ ወታደር ከሞተ ወዲህ ሁለቱ አገራት ያላቸው ግንኙነት ውስብስብ የሚባል ነው።
የሶቪየት ኅብረት መንግሥት በካቡል የሚደግፈውን መንግስት ለማቋቋም ያደረገው ጦርነት ዓለም አቀፍ መገለለልን ያስከተለበት ሲሆን በአውሮፓውያኑ 1989 ደግሞ አፍጋኒስታንን ለቆ እንዲቀጣ አስገድዶታል ሲል ቢበሲ ዘግቧል።
ሰኔ 27 ቀን 2017 ዓ.ም
