የዩክሬን ከፍተኛ የደህንነት ባለስልጣን በመዲናዋ ኪዬቭ በቀን በጥይት መገደላቸውን የአገሪቱ ባለስልጣናት አስታወቁ።
የዩክሬን የሃገር ውስጥ ደህንነት አገልግሎት ከፍተኛ ባለስልጣኑ በመኪና ማቆሚያ ላይ ማንነቱ ያልታወቀ ሰው ተጠግቶ በርካታ ጊዜ በጥይት ከተኮሰባቸው በኋላ ህይወታቸው ማለፉ ተገልጿል።
ጥቃት አድራሹ ከአካባቢው ሸሽቶ ሲሄድ የሚያሳይ ቪዲዮ በማህበራዊ ሚዲያ ተጋርቷል።
የደህንነት ተቋሙ የተገደለበትን ኃላፊ በስም ባይገልጽም የዩክሬን መገናኛ ብዙኃን ኮሎኔል ኢቫን ቮሮንይች እንደሆኑ ዘግበዋል።
የሃገር ውስጥ ደህንነት (ኤስቢዩ) የተሰኘው ተቋም የአገሪቱን ደህንነት እና ስለላዎችን በዋናነት የሚያካሂድ ነው ዘገባው የቢቢሲ ነው።
ሐምሌ 4 ቀን 2017 ዓ.ም
