በትግራይ ክልል ከአንድ ሚሊየን በላይ ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸዉ አልተመለሱም ተባለ።

ከጣቢያችን ጋር ቆይታ ያደረጉት በትግራይ ክልል የማህበራዊና የመልሶ ማቋቋም ኃላፊ አቶገብረስላሴ ታረቀ፤ አብዛኞቹ ተፈናቃዮች ከምዕራብ ትግራይ፣ በኤርትራ ሰራዊት ከተያዙት አካባቢዎች፣ከሰሜን ምዕራብ እና ከተለያዩ የትግራይ አካባቢዎች መሆናቸዉን አንስተዋል።

ተፈናቃዮቹ አሁንም በካምፕ ዉስጥ እንደሚገኙ ገልፀዋል።

የተሰጣቸዉ መጠለያ ድንኳን ከስድስት ወር በላይ መቆየት እንደማይችል ገልፀው ፤አሁን ግን መጠለያ ድንኳኑ ከተቀየረ 4 ዓመት እንዳለፈዉ ተናግረዋል።

ተፈናቃዮች በዚህ ሰዓት በርሃብና በብርድ ምክንያት ህይወታቸዉ እያለፈ እንደሚገኝም ገልፀዋል።

መንግስት ተፈናቃዮቹን እንደ ዜጋ እያያቸዉ አይደለም የሚሉት ኃላፊዉ፤ ችግሮች እንዲፈቱ የሚለመከተዉ አካል ምንም አይነት ጥረት እያደረገ አለመሆኑን ተናግረዋል።

አሁን ያለው ችግር በዕርዳታ የሚፈታ አይደለም የሚሉት ኃላፊዉ፤ ተፈናቃዮቹ ወደ ቀያቸዉ መመለስ እንዳለባቸው እና የፕሪቶሪያዉ የሰላም ስምምነትም ተፈፃሚ መደረግ እንዳለበት ገልጸዋል፡፡

ሊዲያ ደሳለኝ

ሀምሌ 14/2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *