አሜሪካ እና የአውሮፓ ህብረት ከፍተኛ ታሪፍ ለመጀመር ከነሐሴ 1 ቀነ ገደብ ጥቂት ቀናት ቀደም ብሎ ሙሉ በሙሉ የትራንስ አትላንቲክ የንግድ ጦርነትን በማስቀረት ሰፊ የንግድ ስምምነት ላይ ደርሰዋል።
ዉሳኔዉ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን ፕሬዝዳንት ኡርሱላ ቮን ደር ሌየን በስኮትላንድ ካደረጉት የግል ስብሰባ በኋላ የመጣ ነው።
ትራምፕ ‹‹በጣም አስደሳች ድርድር ነበር። ለሁለቱም ወገኖች ጥሩ ይሆናል ብዬ አስባለሁ፤ ‹‹እስካሁን የተደረገው ትልቁ ስምምነት›› ነዉ በማለት ገልፀውታል።
ቮን ደር ሌየን በበኩላቸው ስምምነቱ መረጋጋትን ያመጣል፡፡ በሁለቱም የአትላንቲክ ውቅያኖስ በኩል ላሉ ንግዶቻችን በጣም አስፈላጊ የሆነ ዉጤትን ያመጣል ብለዋል።
የአውሮፓ ህብረት የአሜሪካ ትልቁ የንግድ አጋር ሲሆን፤ባለፈው ዓመት በሸቀጦች እና በአገልግሎቶች መካከል የነበረው የሁለትዮሽ ንግድ ወደ 2 ትሪሊዮን ዶላር የሚጠጋ ነበር።
ሀኒፍ ሀምዛ
ሐምሌ 21/2017 ዓ.ም
