“ካለው ነባራዊ ሁኔታ አንፃር የእስራኤል እና የፍልስጤም ሀገርነት ጉዳይ መፍትሔ ማበጀት አለብን” ሲሉ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ተናገሩ

ተመድ የሁለት ሀገርነት መፍትሔ ጉዳይ ላይ ለመወያየት አስቸኳይ ስብሰባ አካሄደ።

ድርጅቱ የእስራኤልና ፍልስጤምን ውጥረት በዘላቂነት ለመፍታት ያግዛል ባለው የሁለት ሀገርነት መፍትሔ (two state solution) የሁለቱንም ሀገራት ህዝቦች በሉዓላዊ ሀገር የሚኖሩ ሰላማዊ ዜጎች ያደርጋቸዋል ብሏል።

የተመድ ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ “ካለው ነባራዊ ሁኔታ አንፃር የሁለት ሀገርነት መፍትሔን እውን ማድረግ አለብን” ሲሉ ተናግረዋል።

እስራኤልና አሜሪካ፣ እስራኤልና ፍልስጤም ራሳቸውን የቻሉ ሉዓላዊ ሀገራት እንዲሆኑ በሚመክረው ስብሰባ ላይ አልተገኙም ተብሏል።

ስብሰባው የተጠራው በፈረንሳይ እና ሳውዲ አረቢያ አማካኝነት የተጠራ እንደሆነ ተገልጿል ሲል ስካይ ኒውስ ዘግቧል።

ልኡል ወልዴ

ሐምሌ 23/2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *