በአዲስ አበባ ንፋስ ስልክ እና አቃቂ_ቃሊቲ ክፍለ ከተሞች በጎርፍ የበለጠ ተጋላጭ መሆናቸውን ጥናት አሳይቷል።
ከጣቢያችን ጋር ቆይታ ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ የአደጋና ስጋት አመራር ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ በአዲስ አበባ በበልግም ሆነ በክረምት በጣለዉ ዝናብ በሰዉ ላይ ምንም አይነት ጉዳት እንዳላጋጠመ ተናግረዋል።
አቶ ንጋቱ እንደገለፁት በዚህ የክረምት ወቅት የሰዉ ህይወት ማለፍ ባያጋጥምም በከተማዋ መኖሪያ ቤቶች ላይ መጠነኛ ጉዳት እንደተስተናገደ ገልፀዋል።
በቅርቡም በግዮን ሆቴል አካባቢ በተፈጠረ ጎርፍ ምክንያት በተወሰኑ ተሽከሪካሪዎች ላይ መጠነኛ ጉዳት የደረሰ እንደነበር አስታውሰዋል ።
በባለፈዉ 2016 አመት የክረምት ወቅት የስድስት ሰዎች ህይወት ማለፉንም አቶ ንጋቱ ተናግረዋል።
በዘንድሮዉ ክረምት ካለፉት የክረምት ወቅቶች የተለየ የሚያደርገዉ ክረምት ከመግባቱ በፊት የተለያዪ ተጋላጭ የሆኑትን አካባቢዎች በመለየት ከሚመለከታቸዉ አካላት ጋር በመሆን የቅድመ ጥንቃቄ ስራ መሰራቱ ተገልፆል።
አቶ ንጋቱ አሁንም የክረምቱ ወቅት አለማለቁን በማንሳት ህብረተሰቡ ጥንቃቄ እንዲያርግ ሲሉ መልእክት አስተላልፈዋል።
ሊዲያ ደሳለኝ
ነሐሴ 14/2017 ዓ.ም
