ስምምነቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ እና በዳንጎቴ ኢንደስትሪ ኩባንያ መካከል ተፈርሟል፡፡
2.5 ቢሊየን ዶላር ኢንቨስትመንት ፈሰስ የሚደረግበት ይህ ፕሮጀክት፤ ኢትዮጵያ ወደ ምግብ ዋስትና እና የግብርና ትራንስፎርሜሽን በምታደርገው ጉዞ ሊላ ምዕራፍ እንደሆነ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባጋሩት ፅሁፍ ጠቅሰዋል፡፡
“ይህ ፕሮጀክት በሀገር ውስጥ የሥራ እድል ይፈጥራል፣ ለብዙ ገዜ ሲፈተኑ ለነበሩ አርሶ አደሮች አስተማማኝ የማዳበሪያ አቅርቦትን ያረጋግጣል እንዲሁም ለምግብ ሉዓላዊነት ጉዟችን ወሳኝ እርምጃ ነው” ብለዋል፡፡
ነሐሴ 22/2017 ዓ.ም
