የትራም አስተዳደር  ለካማላ ሐሪስ ያደርግ የነበረን ጥበቃ አቆመ።

የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ መንግሥታቸው “ሴክሬት ሰርቪስ” በተባለ ተቋም በኩል ለካማላ ሐሪስ ያደርግ የነበረን ጥበቃ አቆሙ።

የቀድሞዋ ምክትል ፕሬዝደንት በአሜሪካ መንግሥት የሚደረግላቸው ጥበቃ የሚያበቃው በሚቀጥለው ዓመት ነበር።

በሀገሪቱ ሕግ ከኃላፊነታቸው ከተሰናበቱ በኋላ ምክትል ፕሬዝደንቶች ለስድስት ወራት ፕሬዝደንቶች ደግሞ ዕድሜ ልካቸውን ጥበቃ እንደሚደረግላቸው አሶሼትድ ፕሬስ ዘግቧል።

ይሁንና የቀድሞው ፕሬዝደንት ጆ ባይደን ከዋይት ሐውስ ከመሰናበታቸው በፊት በካማላ ሐሪስ ጥያቄ የአሜሪካ ፌድራል መንግሥት የሚያደርግላቸውን ጥበቃ ለተጨማሪ ስድስት ወራት አራዝመው እንደነበር ጉዳዩን የሚያውቁ ሰዎች ለአሶሼትድ ፕሬስ ተናግረዋል። 

የሪፐብሊካን ፓርቲን የወከሉት ዶናልድ ትራምፕ ባለፈው ዓመት በተካሔደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ የዴሞክራት ፓርቲ ዕጩ ሆነው የቀረቡት ካማላ ሐሪስን ማሸነፋቸው አይዘነጋም።

ትራምፕ እርምጃውን የወሰዱት ሐሪስ “107 ቀናት” በሚል ርዕስ ያሳተሙት የሕይወት ታሪካቸውን ለማስተዋወቅ በተዘጋጁበት ወቅት ነው። ሐሪስ ባለፈው ዓመት ፕሬዝደንት ለመሆን ባካሔዱት የምረጡኝ ዘመቻ ላይ የሚያተኩር መጽሀፋቸውን ለማስተዋወቅ ለንደን እና ቶሮንቶን ጨምሮ ወደ 15 ከተሞች ይጓዛሉ።

ነሐሴ 24/2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *