የሲቪል ሰርቪስ ህጉ ተቋማት ለሠራተኞቻቸው ምቹ የህፃናት ማቆያን እንዲያቋቁሙ ቢያስገድድም ይህን ያላደረጉ ተቋማት በርካታ ናቸው ተባለ።

የሴቶችና እናቶችን ማህበራዊ ዋስትና ከማረጋገጥ እንዲሁም የህፃናት ማቆያ ማዕከላት ከሚኖራቸው ሚና አንፃር በበቂ ሁኔታ መስፋፋት አለመቻላቸውን በሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የስርዓተ-ፆታ እና ማህበራዊ ጉዳዮች አካቶ ትግበራ ባለሙያ የሆኑት አቶ ነብዩ ደጀኔ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል።

የህፃናት ማቆያዎችን ትኩረት ሰጥቶ በማስፋፋት ሂደት ውስጥ የግንዛቤ እጥረት እና ብቁ የሰው ሀይል አለመኖር እንደ ችግር የሚጠቀሱ መሆናቸውን ገልፀዋል ።

በሰው ሀይል ዘርፍ ያለውን ክፍተትም ለመሙላት ከአጭር እስከ ረዥም ግዜ የስራ ላይ ስልጠና በዘርፉ ለተሰማሩ ባለሙያዎች እየተሰጠ መሆኑን አቶ ነብዮ ደጀኔ ጠቅሰዋል።

ጉዳዩን በዘላቂነት ለመፍታት ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የህፃናት ማቆያን በብቁ ባለሙያዎች ለማደራጀት የስልጠና ስርዓተ ትምህርት መዘጋጀቱን አንስተዋል።

በፌደራል ደረጃም በሲቪል ሰርቪስ ህጉ መሠረት ከ170 በላይ በመንግሥት ተቋማት የተደራጁ የህፃናት ማቆያ ማዕከላት መኖራቸውን ተናግረዋል።

ሐመረ ፍሬው

መስከረም 12/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *