ኔቶ የአየር ክልል እየጣሰች ነው ያላትን ሩስያን አስጠነቀቀ

የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (NATO) ሩስያ በምሥራቃዊ የአባል አገራቱ ግዛትቶች ላይ ትፈጽማለች ያለውን የአየር ጥሰት እንድታቆም አሳሰበ ።

ኔቶ ጥሰቱ የሚቀጥል ከሆነ አስፈላጊውን ርምጃ እንደሚወስድም ትላንት አስጠነቅቋል ።

ሩስያ ከሰሞኑ ፖላንድ፣ ሩማንያ እና ኤስቶንያ የአየር ክልሎችን መጣሷ ከተሰማ በኋላ ኔቶ በሰጠው ማስጠንቀቂያ ከእንግዲህ የአባል አገራቱ ላይ የሚፈጸሙ ማናቸውንም የአየር ክልል ጥሰቶችን እንደማይታገስ ይፋ አድርጓል ።

ኤስቶኒያ በበኩሏ ባለፈው ዐርብ የታጠቁ የሩስያ የጦር ጄቶች የአየር ክልሏን ለ12 ደቂቃዎች ያህል መጣሳቸው ከተሰማ በኋላ አስቸኳይ ስብሰባ አድርጋ ነበር ።

መስከረም 14/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *