በመዲናዋ ደንብ ተላልፎ የተገኘው የቆዳ ፋብሪካ ድርጅት የ 8 መቶ ሺ ብር ቅጣት ተጥሎበታል።

በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ወረዳ 06 ልዩ ስሙ ቦቼ ሰፈር አካባቢ በኢትዮ ሌዘር ኢንዱስትሪ ስር የሚገኘዉ አዋሽ የቆዳ ፋብሪካ ድርጅት ከፋብሪካው የመነጨ በካይ የፍሳሽ ቆሻሻን ወደ ወንዝ በመልቀቁ 800 ሺህ ብር መቀጣቱን የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ገልፃል።

ድርጅቱ ከዚህ በፊት ተመሳሳይ የደንብ መተላለፍ ፈጽሞ በመገኘቱ 400 ሺህ ብር መቀጣቱን ባለስልጣኑ አስታዉቋል።

ተቋሙ ከጥፋቱ ሳይታረም ያመነጨውን በካይ ፈሳሽ ቆሻሻን በድጋሚ ጨለማን ተገን አድርጎ ወደ ወንዝ ሲለቅ ለባለስልጣኑ በደረሰዉ የማህበረሰብ ጥቆማ መሰረት በደንብ ቁጥር 180/2017 ላይ በተቀመጠው የቅጣት አወሳሰድ እርምጃ በተደጋጋሚ ጥፋት አጥፊ ሆኖ በመገኘቱ 800 ሺህ ብር መቀጣቱን ባለስልጣኑ አስታውቋል።

የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ በጀት መድቦ የወንዝ ዳርቻ የልማት ስራዎችን እየሰራ ባለበት ወቅት እንደዚህ አይነት ተግባር መፈፀም ተገቢ አለመሆኑን የገለጸዉ ባለስልጣኑ ሌሎች ተቋማትም ሆኑ ግለሰቦች ከዚህ እርምጃ መማር እንዳለባቸው አሳስበዋል።

መስከረም 20/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *