በኮንስትራክሽኑ ዘርፍ ካሉ ችግሮች መካከል ሙስና በቀዳሚነት የሚጠቀስ መሆኑን የኢትዮጲያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን አስታወቀ፡፡
የኮንስትራክሽን ኢንድስትሪው በርካታ ገንዘብ እና ሃብት የሚፈስበት በመሆኑ በሰፊው ሙስና የሚፀምበት መሆኑን የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር መስፍን ነገዎ ተናግረዋል፡፡
የዓለም ኢኮኖሚ ፎረም በፈረንጆቹ 2019 ባስጠናው ጥናት፤ በአውሮፓ 46 በመቶ የግንባታው ዘርፍ በሙስና የተበላሸ መሆኑን አረጋግጧል ሲሉ ዋና ዳይሬክተሩ አንስተዋል።
የህግ ማዕቀፍ ችግር ሌላው በዘርፉ የሚታይ ተግዳሮት ነው ያሉ ሲሆን፤ ህጉ በራሱ ቢኖርም አስቻይ ከመሆን ይልቅ ከልካይ የሆነበት እንዲሁም አስፈላጊና ጠቃሚ የሚባሉ የህግ ማዕቀፎች የጎደሉበት ነው ሲሉ ገልፀዋል፡፡
ዶ/ር መስፍን ሌላው በኮንስትራክሽን ኢንድስትሪው ዘርፉ ላይ ማነቆ እንደሆነ የተናገሩት የክህሎት እጥረት መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡
ከከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በዘርፉ ተመርቀው የሚወጡ በርካቶች ቢሆኑም፤የክህሎት ማነስ እና የሙያ ስነ-ምግባር ችግር በሰፊው ይስተዋላል ሲሉ አስረድተዋል፡፡
አቤል እስጢፋኖስ
መስከረም 28/2018 ዓ.ም
