የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ሚንስትር ዶ/ር አለሙ ሲሜ የአሽከርካሪ ባለቤቶች አዲስ በሚለጠፈው የተሽከርካሪዎች ሰሌዳ ላይ የድርጅታቸውን ጨምሮ የራሳቸውን የፈለጉትን ምልክት በሰሌዳቸው ላይ እንዲቀመጥ ማድረግ ይችላሉ ብለዋል።
ባለንብረቶች ቀደም ብለው የፈለጉትን የሰሌዳ ቁጥር በደብዳቤ ጠይቀው ጨረታ ላይ በመሳተፍ መውሰድ ይችላሉ ሲሉም ገልፀዋል።
ሰሌዳው በድርጅቱ ወይንም በግለሰቡ ፍላጎት የሚሰራ በመሆኑ ዋጋው ከመደበኛው የሰሌዳ መስቀየሪያ የተለየ ነው ሲሉም ተናግረዋል።
ከሁለት ወራት በኋላ አዲሱ ሀገር አቀፍ የተሸከርካሪዎች የሰሌዳ ቁጥር(ታርጋ)ተግባራዊ መሆን ሊጀምር መሆኑ መነገሩ ይታወቃል፡፡
ልዑል ወልዴ
መስከረም 29/2018 ዓ.ም
