የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በOBN HORN OF AFRICA TV ሊመጣ ነው

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግን ለማስተላለፍ የኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትዎርክ (OBN)  የሚያስችለውን የምስል መብት  በጨረታ ማሸነፉ  በነገው ዕለት ይፋ ይሆናል ።

ታዲያ በነገው ዕለትም ይፋዊ የስምምነት ፊርማ ከሊጉ አወዳዳሪ ጋር የሚፈራረሙ ሲሆን ከ ቅዳሜ ጥቅምት 8 ጀምሮ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎችን በቀጥታ እንደሚያደርስ ተገልጿል።

የቀጥታ ሰርጭቱ በOBN HORN OF AFRICA በአማርኛ ቋንቋ የሚተላለፍ ሲሆን እንደ አማራጭ በኦሮምኛ ቋንቋም ሊሰራጭ ስለመቻሉ ጣቢያችን ያገኘው መረጃ ያመላክታል።

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ያለፉትን አምስት አመታት DSTV ሲያሰትላልፍ እንድነበር ይታውሳል።

የ2018 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር ጥቅምት 08/2018 እንደሚጀምር ይታወቃል።

በጋዲሳ መገርሳ

ጥቅምት 03/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *