ጤና ሚኒስቴር የውጭ ድጋፎች አሁን ላይ እየቀነሱ ቢመጡም በርካታ አማራጭ መንገዶችን ተጠቅመን እየሰራን ነው አለ፡፡

የውጭ ድጋፍ ሲቀንስ እንደችግር ብቻ ሳይሆን እንደ መልካም አጋጣሚ ተጠቅመን አዳዲስ አቅሞቻችንን ከፍ አድርገን እየሰራን እንገኛለን ሲሉ የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጄ ዱጉማ አስታውቋል፡፡

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ባለፉት አመታት ከበርካታ አጋር ድርጅቶች ጋር ሰፋፊ ስራዎችን ሲሰራ መቆየቱንም ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡

ባለፉት አመታት በጤናው ዘርፍ ከሰሩ አጋር ድርጅቶች ውስጥ አንዱ የሆነው ኔዘርላንድ ሀገር የሚገኘው እና በተለያየ ሀገራት ላይ የሚሰራው “ኮርድኤድ” የሚባል ድርጅት ነው ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው፤ በኛ ሀገር ባለፉት አስርት አመታት በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች ላይ የዜጎችን ጤና ለማሻሻል ትኩረት ሰጥተው ሲሰሩ መቆየታቸውን አንስተዋል፡፡

ተቋሙ መደበኛ የጤና አገልግሎት በስፋት የሌለባቸው አካባቢዎችን መርጦ የተለያዩ ተግባራት ሲያከናውን ነበር ብለዋል፡፡

ዶ/ር ደረጄ ፤ የተወሰኑ ክፍተቶች አሁንም ቢኖሩም በአለም አቀፍ ደረጃ ድጋፎች በቀነሱበት ልክ ሀገራችን ችግር ላይ አልወደቀችም ነዉ ያሉት፡፡

“ኮርድ-ኤድም” ጤና ተቋማት ውጤት ባመጡ ቁጥር ተጨማሪ ፋይናንስ እንዲያገኙ የሚያበረታታ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

በተጨማሪም ለጤናችን የትኛውንም ሀገር ወይም አጋር ድርጅት ሳንጠብቅ በራሳችን የመስራት አቅማችንን ከፍ ማድረግ ያስፈልጋል ሲሉም አሳስበዋል፡፡

ሐመረ ፍሬው

ጥቅምት 05/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *