ሩሲያ በዩክሬን ዋና ከተማ ኪቭ ላይ በፈፀመችው የሚሳኤልና ድሮኖች ጥቃት በሰዎች ላይ የሞት እና የአካል ጉዳት ደረሰ

በዩክሬን ዋና ከተማ ኪቭ በተፈፀመ በዚህ ጥቃት ቢያንስ 3 ሰዎች ሲገደሉ ከ 29 በላይ የሚሆኑ ደግሞ መቁሰላቸው ተገልጿል፡፡

ጥቃቱን ተከትሎ የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ፤ የተፈፀመብን ጥቃት ጠንካራ የአየር መቃወሚያ እንደሚያስፈልግን ማሳያ ነው ብለዋል፡፡

የዩክሬን ጠቅላይ ሚኒስትር በበኩላቸው፤ ጥቃቱ አፀደ ህፃናትን ጨምሮ በሰላማዊ ሰዎች መኖሪያ የተከናወነ ነው፡፡

እንዲሁም በሀይል መሰረተ ልማቶች ላይ ያተኮረ ነበር ያሉ ሲሆን፤ ሩሲያ መጪውን ክረምት በማስመልከት ከፍተኛ ሰብአዊ ቀውስ እንዲፈጠር እየሰራች መሆኑን አስረድተዋል፡፡

የዩክሬን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በበኩላቸው በዲፕሮ፣ ካርኪቭና ሱሚ ግዛቶች ውስጥ በሀይል መሰረተ ልማቶች ላይ ያነጣጠረ ድብደባ መከናወኑን አስታውቀዋል፡፡

የዩክሬን መከላከያ ሚኒስትርም በአገሪቱ ወታደራዊ ኢንዱስትሪዎች ላይ ከባድ ጥቃት መፈፀሙን ይፋ አድርጓል፡፡

ይህንን ጥቃት በማስመልከት ፕሬዝደንት ዘለንስኪ በቴሌግራም ገፃቸው ፤ይሄ ጥቃት ጠንካራ የአየር መቃወሚያ ሲስተም እንደሚያስፈልገን ማሳያ ነው፡፡
የዩክሬንን ከተሞች ከሩሲያ ተደጋጋሚ ጥቃት መከላከል የምንችለው በዚህ ብቻ ነው ብለዋል ሲል የዘገበዉ አልጀዚራ ነዉ፡፡

አቤል እስጢፋኖስ

ጥቅምት 17/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *