የዱዋላ ከተማ ነዋሪዎች ፖል ቢያ ለ8ተኛ የስልጣን ዘመን መመረጣቸዉን ተከትሎ የጀመሩት ተቃዉሞ ለሁለተኛ ቀን መቀጠሉ ተሰምቷል፡፡
ወደ ከተማዋ አንዳንድ ቦታዎች የታጠቁ ሀይሎች መሰማራታቸዉ ተገልጿል፡፡
አሁን በስልጣን ላይ የሚገኙት የ92 ዓመቱ አዛዉንት ፖል ቢያ፤ በድጋሚ መመረጣቸዉን የአገሪቱ የህገመንግስት ምክርቤት ትናንት አሳዉቋል፡፡
ለ8ኛ ዙር የስልጣን ዘመን ፕሬዝዳንት መሆናቸዉን ያረጋገጡት ፕሬዝዳንቱ፤ ከ1982 ጀምሮ አገሪቷን ያለ ተቀናቃኝ መርተዋል፡፡
በተቀናቃኛቸዉ ኢሳ ቲቺሮማ ባካሪ ከፍተኛ ተቃዉሞ የደረሰበት ይህ ዉሳኔ፤ በከፍተኛ ደረጃ ቁጣ እንዲቀሰቀስ ምክንያት ሆኗል፡፡
ፖል ቢያ በሕገ መንግሥት ምክር ቤት የምርጫ አሸናፊ ሆነው የተገለጹ ሲሆን፤ 53.66 በመቶ ድምፅ በማግኘት አሸንፈዋል ተብሏል።
የ92 ዓመቱ አዛዉንት ለ43 ዓመታት በሥልጣን ላይ የቆዩ ሲሆን፤ ስምንተኛ የስልጣን ዘመን ያገኙት ዋና ተፎካካሪያቸውን የቀድሞውን ሚኒስትር ኢሳ ቲቺሮማ ባካሪን በማሸነፍ ነው።
ቲቺሮማ 39.19 በመቶ ድምፅ በማግኘት ሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል።
በዱዋላ የጸጥታ ሁኔታው በመባባሱ የታጠቁ ኃይሎች በከተማዋ በሚገኙ በርካታ ወረዳዎች ተሰማርተዋል ሲል አፍሪካ ኒዉስ አስነብቧል፡፡
እስከዳር ግርማ
ጥቅምት 18/2018 ዓ.ም
