ከ14 ሀገራት የተወጣጡ በእንስሳት ሀብት ላይ የተሰማሩ ኩባንያዎች የሚሳተፉበት አዉደ ርዕይ ተከፈተ

ከ14 ሀገራት የተወጣጡ ከ 90 በላይ አለምአቀፍ የቴክኖሎጂ እና ግብአት አቅራቢዎች እንዲሁም የሀገር ውስጥ ኩባንያዎችም በኤክስፖዉ እንደሚሳተፉበት ተነግሯል።

ይህ አዉደ ርዕይ በእንስሳት መኖ፣ የእንስሳት ጤና፣ የዶሮ እርባታ ፣ በወተት፣ በስጋ እና እንቁላል እንዲሁም በንብ እና በአሳ ሃብት ልማት ዘርፎች ላይ ትኩረት ያደረገ እንደሆነም ሰምተናል።

በተያያዘም 10ኛው የአፍሪካ የእንስሳት እርባታ ኤግዚቢሽንና ኮንግረስ የአሳ ሀብት፣ የንብ እርባታና የባዮ ኢነርጂ ዘርፍ አውደ ርዕይ እንደሚኖርም ተገልጿል።

ለ3ቀናት በሚካሄደው ዓውደ ርዕይና ጉባኤ አጠቃላይ መሰረታቸውን በኢትዮጵያ፣ቻይና፣ ቼክ ሪፐብሊክ፣ፈረንሳይ፣ ጀርመን፣ ህንድ፣ ታንዛኒያ፣ ግብጽ፣ ጣሊያን፣ ብራዚል፣ ኬኒያ፣ ኔዘርላንድስ፣ ቱርክ እና ሶሪያ ያደረጉ አለምአቀፍ የዘርፉ መሪዎች እና ጠንካራ የሀገር ውስጥ ኩባንያዎች እንደሚገኙም ተገልጿል።

ኤክስፖዉ ከጥቅምት 20 እስከ 22 ለሶስት ቀናት በሚሊኒየም አዳራሽ እንደሚካሄድም ተገልጿል።

ለዓለም አሰፋ

ጥቅምት 20/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *