ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በአሜሪካ ታሪክ ረጅሙን የመንግስት መዘጋት የሚያቆመዉን ህግ ፈረሙ

የተቋረጠ የምግብ እርዳታን እንደገና ለማስጀመር፣ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ የፌደራል ሰራተኞችን ደሞዝ ለመክፈል እና የአየር ትራፊክ ቁጥጥር ስርዓትን ለማስጀመር የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ድምጽ ከሰጡ ከሁለት ሰአት በኋላ ዉሳኔዉን ያሳለፉት፡፡

የትራምፕ ከፍተኛ ድጋፍ ያገኘዉ በሪፐብሊካን የሚመራው ምክር ቤት ፓኬጁን 2መቶ22 በ209 በሆነ ድምጽ አጽድቆታል፡፡

የፌደራል የጤና መድህን ድጎማዎችን ለማራዘም ስምምነት ላይ ለመደረስ ባለመቻሉ የተናደዱ ዴሞክራቶች ከፍተኛ ተቃውሞ ቢያሰሙም ዉሳኔዉ መጽደቁ ነዉ የተገለጸዉ፡፡

ትራምፕ ሴኔቱ ያሳለፈውን ረቂቅ ህግ መፈረማቸውን ተከትሎ ለ43 ቀናት ስራ ያቆሙ የፌደራል ሰራተኞችን ከዛሬ ጀምሮ ወደ ስራቸው ይመለሳሉ የተባለ ሲሆን፤ ሙሉ የመንግስት አገልግሎቶች እና ስራዎች በምን ያህል ፍጥነት ሊመለሱ እንደሚችሉ ግን ግልጽ አልሆነም፡፡

በዚህም ምክንያት የገንዘብ ድጋፉ እስከ ጥር 30 ድረስ የሚራዘም ይሆናል፡፡

ይህም የፌደራል መንግስት ካለበት የ38 ትሪሊየን ዕዳ ላይ በየዓመቱ 1.8 ትሪሊዮን ዶላር ዕዳ እንዲጨምር ያደርገዋል ሲል የዘገበዉ ሮይተርስ ነዉ።

እስከዳር ግርማ

ህዳር 04/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *