ከኢትዮጵያ የወጣው የእሳተ ገሞራ ፍንዳታ ቀይ ባህርን በመሻገር ኦማን እና የመንን አቋርጦ የህንድ ዋና ከተማ ደልሂ ደርሷል።
ፍንዳታው የተከሰተው በኢትዮጲያ አፋር ክልል ሃይሊ ጉቢ አካባቢ ሲሆን እሳተ ገሞራው ለብዙ ሺህ ዓመታት ተዳፍኖ የኖረው ነው፤ ይህ ተዳፍኖ የኖረ እሳት ገሞራ እሁድ ማለዳ የተነቃቃ ሲሆን ፍንዳታው የለቀቀው አመድ በሺ የሚቆጠሩ ሜትሮችን ተጉዞ ወደ ከባቢ አየር ውስጥ ገብቱዋል።
በህንድ ውስጥ በአመዱ ምክንያት በርካታ አለም አቀፍ እና የሀገር ውስጥ በረራዎች የተሰረዙ ሲሆን ፣ በርካታ በለራዎችም ከመነሻ ሰአታቸው ዘግይተዋል አቅጣጫም ቀይረዋል የሀገሪቱ የአቪዬሽን ተቆጣጣሪ አየር መንገዶች በአመዱ ከተጎዱ አካባቢዎች እንዲርቁ በጥብቅ አሳስቡዋል፡፡
ባለሙያዎች እንደተናገሩት ከሆነ እስካሁን የአመድ ብክለት ደረጃው ግልፅ አይደለም፤ ነገር ግን ማክሰኞ እለት እንደተገለጸው ቀድሞውኑ “በጣም ደካማ” የሆነውን የዴሊ አየር ተጽዕኖ ሊያሳድርበት አይችልም ።
የእሳተ ገሞራ አመድ በእሳተ ገሞራ ፍንዳታ ወቅት ወደ ከባቢ አየር ውስጥ የሚለቀቁ ጥቃቅን እና የሚበላሹ ቅንጣቶች ደመና ነው። የአውሮፕላን ሞተሮችን ሊጎዳ፣ የአየር ማረፊያዎችን ሊበክል እና እይታን ሊቀንስ ይችላል፣ ይህም ለበረራ ስራዎች አደገኛ ያደርገዋል።
የሕንድ የሚቲዎሮሎጂ ዲፓርትመንት (አይኤምዲ) ዋና ዳይሬክተር ሚሩትዩንጃይ ሞሃፓትራ “በ አመዱ የተጎዳው አካባቢ ከፍታ በ8.5 ኪ.ሜ (5.2 ማይል) እና ከባህር ጠለል በላይ በ15 ኪሎ ሜትር መካከል ነው” ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል።
በተጨማሪም ሚስተር ሞሃፓትራ ” አመዱ ለጊዜው የሳተላይት ተግባራትን እና የበረራ ስራዎችን ያስጓጉላል፤ ነገር ግን የአየር ሁኔታን ወይም የአየር ጥራትን ሊነካ አይችልም፤ትላንትና ማምሰሻውን ወደ ሰሜን ህንድ ደርሶ ነበር ያሉት ወደ ቻይና የሚያመራ ይመስላል” ብለዋል ፡፡
እንደ ስካይሜት የአየር ሁኔታ ገለፃ የግል ኤጀንሲ እንዳለው አመዱ ለመበተን ምን ያህል ጊዜ እንደሚፈጅ ለመተንበይ አስቸጋሪ ቢሆንም፣ አይኤምዲ ግን የዴሊ ሰማይ እስከ ማክሰኞ ምሽት ድረስ መጥራት እንዳለበት ተንብዩዋል።
የእሳተ ገሞራ አመድ ደመና የመከሠት እድሉ ዝቅተኛ ነው፤ ነገር ግን በታሪክ በ2010 የአይስላንድ ኢይጃፍጃላጆኩል እሳተ ገሞራ ሲፈነዳ፣ ዓለም አቀፍ የጉዞ ትርምስን አስከትሎ ነበር። የዩናይትድ ኪንግደም እና የአውሮፓ አየር ክልል ተዘግቷ ይህም ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወዲህ አስከፊው የአየር ጉዞ መስተጓጎል ምክንያት ነበር ሲል የዘገበው BBC ነው ።
ሀና ሰይፉ
ህዳር 16/2018 ዓ.ም
