የማይክሮ ፋይናንስ ተቋማትን ከብሔራዊ ዲጂታል ሥነ-ምህዳር ጋር ለማዋሃድ እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ

አሪፍ ፋይናንሺያል ቴክኖሎጂስ ከኢትዮጵያ ፊንቴክ ኢንዱስትሪ ትራንስፎርሜሽን ፎረም ጋር በመተባበር በዲኦሎፖል ሆቴል የማይክሮ ፋይናንስ ጉባኤ አካሂዷል።

የጉባኤው ትኩረት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን እና የገጠር ዜጎችን የሚያገለግሉትን የኢትዮጵያን ወሳኝ የማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት ከብሔራዊ ዲጂታል ሥነ-ምህዳር ጋር ማዋሃድ እንደሆነ ተገልጿል።

ተቋሟቱን ከዲጂታል ጋር የማስተሳሰር ስራው በአሪፍፔይ እየተሰራ ሲሆን ከስራዎቹ መካከል የአሪፋይ ኤምኤፍአይ ስዊች (MFI Switch) አንዱ መሆኑ ተነግሯል።

ይህ አዲስ፣ ጠንካራ እና ደህንነቱ የተጠበቀ መሠረተ ልማት ሁሉንም የማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት ያለምንም እንከን ከብሔራዊ የክፍያ አውታረ መረብ ጋር ለማገናኘት የተነደፈ ነው።

የአሪፍፔይ ዲጂታል ዋሌት የማይክሮ ፋይናንስ ደንበኞች ሂሳባቸውን እንዲያስተዳድሩ፣ ብድር እንዲቀበሉ እና በዲጂታል መንገድ ክፍያዎችን እንዲፈጽሙ የሚያስችል መሆኑ ተነግሯል።

አሪፍፔይ በአሁኑ ወቅት ከ120 በላይ ሰራተኛ ይዞ በቀን እስከ 680 ሚሊዮን ብር በአሪፍፔይ በኩል እየተንቀሳቀሰ የሚገኝበት ፋይናንሺያል ቴክኖሎጂ ድርጅት ነው።

አቤል እስጢፋኖስ

ህዳር 16/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *