ይህንን ያስታወቀው የአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮ ነው።የቢሮው ሀላፊ ወይዘሮ ሀቢባ ሲራጅ እና ሌሎች የቢሮዉ ሀላፊዎች በመርካቶ ገበያ ተገኝተዉ የንግድ እንቅስቃሴ ምልከታ ማድረጋቸውን ንግድ ቢሮው አመልክቷል።
ከተደረገው ምልከታ በኋላ ሀላፊዋ የምግብ ዘይት እጥረት ችግር እንዳለ በማህበራዊ ሚዲያ የሚናፈሰዉ ወሬ ሀሰተኛ ነዉ ብለዋል።
በተጨማሪም ምርትን በመከዘን ሰዉ ሰራሽ የምርት እጥረትን የሚፈጥሩ ነጋዴዎች ላይ ቢሮዉ ተጨባጭ እርምጃን ይወስዳል ነው ያሉት።
በ እለቱም የምግብ ዘይትን በመከዘን ሰዉ ሰራሽ የምርት እጥረት ለመፍጠር የሞከሩ ከ20 በላይ ተሳቢዎች ምርቶቻቸዉ ወደ ገበያ እንዲሰራጭ መደረጉን ገልፀዋል።
አቤል እስጢፋኖስ
ህዳር 22/2018 ዓ.ም
