በኢትዮጵያ 70 በመቶ የሚሆኑ የአጥንት ታካሚዎች ወደ ባህላዊ ወጌሻ ሕክምና ይሔዳሉ ተባለ።

በአገራችን ከ40 እስከ 70 በመቶ የሚሆኑ የአጥንት ታካሚዎች ወደ ባህላዊ ህክምና ይሄዳሉ ነዉ የተባለዉ፡፡

በአጥንት እና አጥንት ጉዳቶች ላይ የሚሰራው ‹‹ቦሳድ›› የተሰኘ ቡድን አደረግኩት ባለዉ ጥናት፤ ወደ ባህላዊ ህክምና የሚሄዱ የማህበረሰብ ክፍሎች ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው፣ በገጠራማው ክፍል የሚኖሩ ዜጎች ፣የግንዛቤ እጥረት ያለባቸውና ሕፃናት እንደሆኑ በጥናቱ ለይቷል።

ጥናቱ የተካሔደዉ አዲስ አበባ እና ድሬዳዋን ጨምሮ ባህር ዳር፣ ጎንደር፣ ጅማ፣ ዋቻሞ፣ ሐዋሳ፣ ሐረማያ፣ አሰላ እና ጅግጅጋ በሚገኙ የዩኒቨርሲቲ ሆስፒታሎች ውስጥ ሲሆን፤ በአጠቃላይ 10 ክልሎችን አካቷል።

78 በመቶ የሚሆኑት የጎንዮሽ ጉዳት እንደደረሰባቸውም በጥናቱ ተመላክቷል፡፡

26 በመቶ የሚሆኑት ደግሞ ወደ ጤና ተቋማት መጥተው ህክምና ከጀመሩ በኋላ ተመልሰው ወደ ባህላዊ ህክምና የሄዱ መሆናቸው በጥናቱ ተለይቷል፡፡

ህፃናት ለአጥንት ጉዳቶች ተጋላጭ መሆኑን ያመላከተዉ ጥናቱ፤ በዚህም 78 በመቶ የሚሆኑት በትምህርት ቤት አካባቢ የሚጎዱ መሆናቸውን ገልጿል።

የችግሩ ዋነኛ ምክንያት በጤና ተቋማት ያለው ክፍተት እና በባህላዊ ህክምና ውስጥ የሚታየው የአሰራር ስህተት እንደሆነም ተገልጿል።

ችግሩን ለመቅረፍ ማህበሩ የህብረተሰብ አቀፍ አገልግሎቶቹን ለማጠናከር ከሁሉም ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት ለመስራት ጥሪ አቅርቧል፡፡

ሊዲያ ደሳለኝ

ህዳር 22/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *