ሜታ የአውስትራሊያ ታዳጊ ልጆችን ከኢንስታግራም እና ፌስቡክ ማስወጣት ጀመረ

ሜታ ከ16 አመት በታች የሆናቸው የአውስትራሊያ ልጆችን ከኢንስታግራም፣ ፌስቡክ እና ትሬድስ መተግበሪያዎች ላይ ማስወጣት ጀምሯል፡፡

ይህ የሆነው የወጣቶች ይፋዊ የማህበራዊ ሚዲያ እገዳ ከመጀመሩ አንድ ሳምንት በፊት ነው።

ግዙፉ የቴክኖሎጂ ኩባንያ ከታህሳስ 4 ጀምሮ ከ13 እስከ 15 ዓመት የሆናቸው ተጠቃሚዎች መለያቸውን መዝጋት እንደሚጀምር አሳውቆ ነበር፡፡

በግምት 1መቶ50ሺህ የፌስቡክ ተጠቃሚዎች እና 3መቶ50ሺህ የሚሆኑ የኢንስታግራም አካውንቶች ይዘጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

አውስትራሊያ ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎችን ከማኅበራዊ ሚዲያ ማገዷን ተከትሎ ከግዙፍ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ለሚደርስባት ጫና እንደማትበገር አስታወቀች።

ከቢቢሲ ጋር ቆይታ ያደረጉት የአውስትራሊያ የኮሚዩኒኬሽን ሚኒስትር አኒካ ዌልስ “የቆምነው ለወላጆች ነው እንጂ ለግዙፍ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች አይደለም” ብለዋል።

የፌስቡክ አስተዳዳሪ ሜታ፤ የታዳጊዎችን የበይነ መረብ ደኅንነት መጠበቅ መልካም ቢሆንም፤ እገዳ መጣል መፍትሔ እንደማያመጣ ገልጿል።

በዓለም የመጀመሪያው የማህበራዊ ሚዲያ እገዳ ታኅሣሥ 10 በአውስትራሊያ ይጀምራል፣ ኩባንያዎች ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ልጆች አካውንት እንዳይኖራቸው ለማቆም “ሀላፊነት የተሞላው እርምጃ” ካልወሰዱ እስከ 33 ሚሊየን የሚደርስ የአሜሪካ ዶላር ቅጣት ይጠብቃቸዋል።

የሜታ ቃል አቀባይ ለቢቢሲ እንደተናገሩት “ህጉን ማክበር ቀጣይነት ያለው እና ባለ ብዙ ሽፋን ሂደት ይሆናል” ብለዋል።

በተጨማሪም “ሜታ ህጉን ለማክበር ቁርጠኛ ቢሆንም የበለጠ ውጤታማ እንዲሆን ደረጃውን የጠበቀ እና ግላዊነትን የሚጠብቅ አካሄድ እንደሚያስፈልግ እናምናለን” ብለዋል።

ታዳጊዎችን ከማኅበራዊ ሚዲያ ያገደችው አውስትራሊያ በግዙፍ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ጫና ውሳኔዋን እንደማትቀይርም ገልጻለች፡፡

አንዳንድ ባለሙያዎችም የእገዳው ውጤታማነት ላይ ጥያቄ አንስተዋል።

በአለም ላይ በዓይነቱ የመጀመሪያ የሆነውን የአውስትራሊያ የማህበራዊ ሚዲያ እገዳ አለም አቀፍ መሪዎች በቅርበት እየተከታተሉት ይገኛሉ።

ሀና ሰይፉ

ህዳር 25/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *