ትራምፕ የዩክሬኑ መሪ የቅርብ ጊዜውን የሰላም ዕቅድ አላነበቡትም ሲሉ ተናገሩ

ከትራምፕ ንግግር በኋላ ዘሌንስኪ ለለንደን ውይይት ተሰናድተዋል ተብሏል፡፡

የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ በዩክሬን ያለውን ጦርነት ለማስቆም በአሜሪካ የሚደረገዉ ግፊት በቀጠለበት በአሁኑ ወቅት ቁልፍ የአውሮፓ አጋሮችን በለንደን ያገኛሉ ነዉ የተባለዉ፡፡

ባለፈው ሳምንት የዩክሬን ባለስልጣናት ለሶስት ቀናት ድርድር በፍሎሪዳ ከአሜሪካ ተደራዳሪዎች ጋር ተገናኝተው ነበር፡፡

በወቅቱ የዜለንስኪ ዋና ተደራዳሪ የሩሲያን ጥቅም ያስቀድማል ተብሎ በሚታሰበው በዋይት ሀውስ ዕቅድ ላይ ለውጦች እንዲኖሩ ግፊት አድርጓል፡፡

በወቅቱ ሁለቱም ወገኖች መሻሻል እንዳለ ቢናገሩም፤ እነዚያን ንግግሮች ተከትሎ የአሜሪካዉ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በዜለንስኪ ቅር ተሰኝቻለሁ፤ የሰላም ዕቅድ ሃሳቡን እስካሁን አላነበበውም በማለት ተናግረዋል፡፡

ዛሬ ዜለንስኪ ከእንግሊዙ ጠቅላይ ሚኒስትር ኬር ስታርመር፣ ከፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን እና ከጀርመን ቻንስለር ፍሬድሪክ ሜርዝ ጋር ይገናኛሉ ሲል የዘገበው ቢቢሲ ነው።

ሀና ሰይፉ

ህዳር 29/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *