ይህም የቀጣዩን ትውልድ ዐቅም በሳይንስ እና ቴክኖሎጂ እንዲሁም በምኅንድስና እና ሒሳብ ዘርፍ ለማጎልበት የሚያስችል ነው::
ዓለም አቀፋዊ የቴክኖሎጂ ተቋም የሆነው ያንጎ ግሩፕ፣ የያንጎ ፌሎውሺፕ ቀጣይ ምዕራፍ – በመላው አፍሪካ የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ እንዲሁም የምኅንድስና እና ሒሳብ ዘርፍ ችሎታን ለማጎልበት ዓልሞ እንደተነደፈ አስታውቋል።
ያንጎ ፌሎውሺፕ፣ ወጣቶችን በማማከር እና አቅጣጫ በመጠቆም እንዲሁም ግብዓቶችን እና የግንኙነት መረቦችን በመዘርጋት፣ ተሳታፊዎች ማኅበረሰባቸውን የሚጠቅሙ ሐሳቦችን እንዲያመነጩ ብሎም ወደ ተግባር እንዲቀይሩ እገዛ ያደርጋል።
በዛምቢያ እና በአይቮሪኮስት በተሳካ ሁኔታ የተጀመረው የያንጎ ፌሎውሺፕ ፕሮግራም አድማሱን በማስፋት ወደ አራት ተጨማሪ ሀገራት፣ ማለትም ኢትዮጵያ፣ ሞዛምቢክ፣ ጋና እና ሴኔጋል ደርሷል።
መርሐ ግብሩ፣ የመጨረሻ ዓመት ተማሪዎቹን፣ በወደፊት የሥራ ሕይወታቸው ውጤታማ እንዲሆኑ የሚያስችሉ ድንቅ የሥራ ልምዶች እና ክሂሎቶችን እንዲያገኙ በማመቻቸት ለስኬታማ ነገአቸው ዝግጁ ካደረገ በኋላ፣ በቀጣዩ ዓመት ደግሞ አዳዲስ ስኬታማ ባለሙያዎችን እና በድንበር የማይገደብ የተግባቦት መረብን በመፍጠር ከአፍሪካ ልዩ ልዩ አካባቢዎች የተውጣጡ ወጣቶችን በዐቅም ለማጎልበት ዝግጅቱን ጨርሷል፡፡
ፕሮግራሙ ትብብርን፣ ፈጠራን እና ብቃት ያለው አመራርን የሚያበረታታ ሲሆን አህጉሪቱን የሚያጠቃልልና የቀድሞ ተማሪዎችን የሚያሳትፍ ጠንካራ አውታረ መረብ በመገንባት ላይ ይገኛል ተብሏል።
የያንጎ የአካባቢ ማዕከሎች፣ ስኬታማ ወጣቶችን በማስተማር እና በዐቅም በማጎልበት ቁልፍ ሚናን ይጫወታሉ፡፡ ይህም ፕሮግራሙ ችሎታንና እና አካባቢያዊ ሥነ-ምኅዳርን እንደሚያጠናክር የሚናገር ነው።
ታህሳስ 10/2018 ዓ.ም
