የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም በያዝነው አመት 30 ሚሊየን ሴቶችን ተደራሽ ለማድረግ ከሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ያዘጋጀዉን ፕሮግራም በይፋ ተጀምሯል፡፡
የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዲዔታ ሂክማ ኸይረዲን፥ ከዚህ ቀደም ሴቶች ከመታወቅ መብታቸው ተገልለው የመታወቂያ ባለቤት የነበሩት ጥቂቶች ብቻ እንደነበሩ አንስተው ፤ በዚህ ሳቢያ በፍትሕ እና ፋይናንስ ዘርፎች ተጠቃሚ ሳንሆን ቀርተናል ብለዋል።
የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ዋና አስተባባሪ አቶ ዮዳሔ አርአያስላሴ፤የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ለሥርዓተ ፆታ እኩልነት መረጋገጥ መሠረት ሆኖ የሚያገለግል ነው ብለዉ ፤30 ሚሊየን ሴቶችን የፋይዳ ምዝገባ ለማካሄድ ስራ አስጀምረናል ነዉ ያሉት፡፡
አካል ጉዳተኞች፣ ህፃናትና ሌሎች ተጋላጭ የማህበረሰብ ክፍሎችን የመታወቅ መብታቸው እንዲረጋገጥ በማድረግ አካታችነት እንዲጎለብት የማድረግ ተግባር ሀላፊነትን ወስደን ስራዉን አስጀምረናል ብለዋል።
ታህሳስ 10/2018 ዓ.ም
