በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 3 ሺህ 4መቶ22 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል ያለዉ የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ነዉ፡፡
ሚኒስቴሩ እንዳለዉ፤በሳምንቱ ውስጥ በተደረገ 14 ዙር በረራ የተመለሱት 3ሺህ 3መቶ37 ወንዶችና 82 ሴቶች እንዲሁም 3 ህፃናት ሲሆኑ፤ ከተመላሾች መካከል 72 እድሜያቸው ከአስራ ስምንት አመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ይገኙበታል።
መስከረም 5/ 2018 በተጀመረው ዜጎችን ወደ ሀገር ቤት የመመለስ ስራ እስካሁን 45 ሺህ 93 ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገር መመለስ ተችሏል።
ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከሚመለከታቸው ባለድርሻና አጋር አካላት ጋር በመቀናጀት ለተመላሽ ዜጎች በአየር ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ የማድረግ እና ከቤተሰብ ጋር የማቀላቀል ስራም በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ አስታዉቋል፡፡
ጥር 18/2018 ዓ.ም
