በኦሮሚያ ክልል የተወሰኑ አካባቢዎች የሴት ልጅ ግርዛት በስፋት እየታየ ነዉ ተባለ

ይህንን ያለዉ “Young lives” የተባለ መንግስታዊ ያልሆነ ተቋም በዛሬዉ እለት ይፋ ባደረገዉ የጥናት ዉጤቱ ነዉ።

በተለይም ጥናቱ በቀዉስ ዉስጥ ያለፉ ወጣቶች ህይወት ዙሪያ ትኩረቱን ያደረገ ሲሆን በ ሰባት ያህል ነጥቦች ዙሪያ ጥናቱን ማካሄዱን ተናግሯል።

ከነጥቦች መካከል የሆነዉ የሴት ልጅ ግርዛት እና ያለ እድሜ ጋብቻ ዙሪያ በጥናቱ የተሳተፉት ናርዶስ ጮታ ከጣቢያችን ጋር ባደረጉት ቆይታ ስለ ግኝቱ ነግረዉናል።

ተመራማሪዋ እንደሚገልፁት ጥናቱ ትኩረት ካደረገበት አንዱ የሆነዉ ኦሮሚያ ክልል መሆኑን ተናግረዉ እስካሁን የሴት ልጅ ግርዛት የሚታይበት መሆኑን ይገልፃሉ።

በክልሉ አብዛኛዎቹ አካባቢዎች ሴቶች ወደ 13 እና 14 አመት የእድሜ ክልል አካባቢ እንደሚገረዙ ለማወቅ ተችሏል ብለዋል።

በማህበረሰቡ ዘንድ እንደ አስፈላጊ ነገር ነዉ የሚታየዉ ያሉት ተመራማሪዋ ይህ ድርጊት ለትዳር ያዘጋጃታል ብለዉ እንደሚያምኑ መረዳት ተችሏል ይላሉ።

በዚህም ይሄ ድርጊት ቀጥሎ መስተዋሉን ነግረዉናል።

ማህበረሰቡ ድርጊቱን መፈፀም በህግ እንደሚያስጠይቅ ቢያወቅም አንድ ሴት ልጅ ሳትገረዝ በመቅረቷ በማህበረሰቡ ዘንድ ያላት ቅቡልነት እና ድርሻ ያነሰ እንደሚያደርገዉ ለማወቅ መቻሉን ተናግረዋል።

በሴቶቹም ዘንድ በማህበረሰቡ ዘንድ ተቀባይነት ላለማጣት መገረዙን እንደሚፈልጉት ተመራማሪዋ ይገልፃሉ።

ግንዛቤን ለመፍጠር በአካባቢያቸው ለአቻ ለአቻ ቡድኖች ስራዎች ለዉጥ ለማሳየት ቢጥሩም ጠንካራ አለመሆኗቸዉን ለማወቅ ተችሏል ብለዋል።

በዚህ ጥናት ዉስጥ ጥናቱ ሲጀምር ጀምሮ ከተካተቱ ህፃናት ዉስጥ አንድ አምስተኛ ያህሉ ከ18 አመት በታች ስለማግባታቸዉ ከመድረኩ ሰምተናል።

ቁምነገር አየለ

ጥር 21/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *