ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ በ6ኛው የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 10ኛ መደበኛ ስብሰባ ተገኝተዉ ከምክር ቤቱ አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ እየሰጡ ይገኛል፡፡
በዚህ ወቅት‹‹እኔ የተሻለ ምርጫ ይኖራል ብዬ አስባለሁ፤አንዳንዶች ግን ለምርጫው ስጋት አለባቸዉ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ለኢትዮጲያ ህዝብ መልሴ በውጤት እንየው ነው›› ሲሉ ተናግረዋል፡፡
በእርግጠኝነት ግን አሁን ካሉ ሰዎች አምስት አስር እጥፍ ልዩ ድምፆች ፓርላማ ውስጥ እንደሚሳተፉ ጥርጥር የለኝም ሲሉ ቅድመ ግምታቸውን አስቀምጠዋል፡፡
መንግስት ስራውን እርግፍ አድርጎ ትቶ ምርጫ ላይ ጊዜውን እና ገንዘቡን እያባከነ ነው ተብሎ ከምክርቤቱ አባላት ለተነሳላቸው ጥያቄ መልስ የሰጡት ጠ/ሚ ዐብይ፤ የኛ አባል መሆናችሁን ዘነጋችሁት እንዴ ምርጫውን ትታችሁ ቀን ከለሊት ኮሪደር ትላላችሁ እያለ ነው ሲሉ አንስተዋል፡፡
በሃገራት የምርጫ አመት ሃገራዊ እድገት መቀነስ እንደሚመዘገብ የጠቀሱት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ፤ በእኛ ሃገር ግን እድገት እየተመዘገበ መሆኑ እየሰራ ያለ መንግስት መኖሩን ማሳያ ነው ብለዋል፡፡
ምርጫው በሰላም ይከናወናል፤ በምርጫ የሚሳተፉ ሃይሎችም ተጠቃሚ ይሆናሉ ሲሉ ለምክር ቤት አባላት ተናግረዋል።
አቤል እስጢፋኖስ
ጥር 26/2018 ዓ.ም
