የፕሬዝደንት ትራምፕ የሰላም ቦርድ የሱዳንን ጦርነት ለማስቆም የሚያስችል አዲስ እቅድ በሚቀጥለው ወር ይፋ እንደሚያደርግ ተገለጸ።

ሱዳን ትሪቢዩን የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን ጠቅሶ እንደዘገበው፣ በጥር 15 በአለም ኢኮኖሚ ፎረም ላይ የተመሰረተው ይህ ቦርድ፣ በሱዳን ፖለቲካዊና ደህንነታዊ ማሻሻያዎችን ለማምጣት አቅዷል።

የእቅዱ ዋና አካል አክራሪ ኃይሎችን ከወታደራዊና ከመንግስት መዋቅር ውስጥ ማስወጣት ሲሆን፣ ወዲያውኑ ተግባራዊ የሚሆን የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ ለመድረስም ጥረት ይደረጋል።

በተጨማሪም ጦርነቱ ያስከተለውን ቀውስ ለመታደግ ዓለም አቀፍ የሰብአዊነት ኮንፈረንስ የማዘጋጀት ፍላጎት እንዳለ ተመልክቷል።

ይህ የአሜሪካ እቅድ ከሳዑዲ አረቢያ፣ ከግብፅና ከዩናይትድ አረብ ኤምሬትስ ሙሉ ድጋፍ ያገኘ ሲሆን፣ ባለፈው ወር የአሜሪካ ባለስልጣናት በእነዚህ ሀገራት ጉብኝት ማድረጋቸው ይታወሳል።

ይሁንና የሱዳን ተፋላሚ ወገኖች በእቅዱ ላይ ስላላቸው አቋም እስካሁን የተገለጸ ነገር የለም። ምንም እንኳን የቦርዱ ቀዳሚ ትኩረት የጋዛን ቀውስ መፍታት ቢሆንም፣ በመመስረቻ ቻርተሩ ላይ በየትኛውም የዓለም ክፍል ግጭቶችን የማስወገድ ዓላማ እንዳለው ሰፍሯል።

አቤል እስጤፋኖስ

ጥር 28/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *