ቶተንሃም ሆትስፐር አሰልጣኝ ቶማስ ፍራንክን ከኃላፊነታቸው ማሰናበቱን አስታወቀ

ዴንማርካዊው በክለቡ ለስምንት ወራት ብቻ ከቆዩ በኋላ የተሰናበቱት ትናንት ምሽት በገዛ ሜዳቸው በኒውካስል 2-1 በሆነ ውጤት መሸነፋቸውን ተከትሎ ነው።

ቶተነሀም በአሁኑ ወቅት በፕሪምየር ሊጉ 16ኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ ሲሆን፤ ከወራጅ ቀጠናው የራቀው በ5 ነጥብ ብቻ ነው።

ክለቡ ባለፉት 8 የሊግ ጨዋታዎች ምንም ድል አላስመዘገበም። ይህም ከጥቅምት 2008 ወዲህ ያስመዘገበው ረጅሙ ድል አልባ ጉዞው ነው።

ባለፉት 17 የሊግ ጨዋታዎች ማሸነፍ የቻሉት በሁለቱ ብቻ ሲሆን፣ ማግኘት ከሚገባቸው 52 ነጥቦች ውስጥ 12ቱን ብቻ ነው የሰበሰቡት።

ቶማስ ፍራንክ በቶተነሀም አንዠ ፖስትኮግሉን ተክተው ስራ የጀመሩት በሰኔ ወር ነበር።
እስከ 2028 የሚያቆይ ኮንትራት ቢኖራቸውም በሊጉ እያሳዩ ያሉትን ደካማ አፈጻጸም መቀልበስ ባለመቻላቸው ተሰናብተዋል።

ቶተነሃም ምንም እንኳን በሊጉ ደካማ ቢሆንም በሻምፒዮንስ ሊጉ የምድብ ጨዋታ ግን 4ኛ በመውጣት በቀጥታ ወደ 16ቱ ውስጥ መግባቱ የሚታወስ ነው ።
ሆኖም በካራባኦ ካፕ እና በኤፍ ኤ ካፕ ቀደም ብለው መሰናበታቸው ለአሰልጣኝ ቶማስ ፍራንክ ስንብት ተጨማሪ ምክንያት ሆኗል።

ምስጋናው ታደሰ

የካቲት 04/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *