የወር አበባ ንፅህና መጠበቂያ ምርቶች ከቀረጥ ነፃ እንዲገቡ የሚያስችል ሀገር አቀፍ ጥናት እየተካሄደ ነው ተባለ

የተዋልዶ ጤና አገልግሎት ሰጭ ድርጅቶች ማህበራት ህብረት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ አበበ ከበደ፥የሴት ተማሪዎችን የትምህርት ተሳትፎ ለማሳደግና ጤናቸውን ለመጠበቅ የወር አበባ ንፅህና መጠበቂያ ምርቶች ከቀረጥ ነፃ ወደ ሀገር ውስጥ እንዲገቡ የሚያስችል የፖሊሲ ጥናት እየተካሄደ መሆኑን ተናግረዋል።

ምርቶቹ በገበያ ላይ ያላቸው ዋጋ ከፍተኛ መሆን በርካታ ታዳጊዎችን ከትምህርት ገበታቸው እንዲቀሩ እያደረገ መሆኑን አንስተዋል።

ህብረቱ ምርቶቹ ከቀረጥ ነፃ ቢገቡ በሀገር ኢኮኖሚና ማህበራዊ ህይወት ላይ የሚያመጡትን አዎንታዊ ተጽዕኖ የሚያሳይ ጥናት እያካሄደ መሆኑን ገልፀዋል።

ጥናቱ ሲጠናቀቅ ለመንግስት በተለይም ለገንዘብ ሚኒስቴር ቀርቦ ውሳኔ እንዲያገኝ ጥረት ይደረጋል ብለዋል።

ሊዲያ ደሳለኝ

የካቲት 17/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *