እንደ ኳታር መከላከያ ሚኒስቴር መግለጫ ከሆነ፤ በኳታር ግዛት ውስጥ ሁለት የኢራን ባሊስቲክ ሚሳይሎች ጥቃት ሰንዝረዋል።
ከጥቃቱ ጋር በተያያዘ የወጡ ዝርዝር መረጃዎች እንደሚያሳዩት፤ አንደኛው ሚሳዔል በመካከለኛው ምስራቅ ትልቁ የአሜሪካ የጦር ሰፈር በሆነው በአል ኡደይድ የአየር ኃይል ጣቢያ ላይ አርፏል።
ሁለተኛው ሚሳዔል ደግሞ በኳታር የአየር መከላከያ ሚሳይል መቃወሚያ ሥርዓት አማካኝነት በአየር ላይ እንዲከሽፍ ተደርጓል።
የኳታር መንግሥት እንደገለጸው፤በጥቃቱ ምክንያት እስካሁን ድረስ የደረሰ የሰው ሕይወት መጥፋትም ሆነ የአካል ጉዳት የለም።
እንዲህ ያሉ ክስተቶች በቀጣናው ያለውን የጂኦፖለቲካዊ ውጥረት ሊያባብሱ እንደሚችሉ ይገመታል።
ሀና ሰይፉ
የካቲት 25/2018 ዓ.ም
