በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በማዕድን ቁፋሮ ቦታ በደረሰ የመሬት መንሸራተት የሟቾች ቁጥር ከ200 በላይ መድረሱ ተገለጸ

በምሥራቃዊ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በሚገኝ የማዕድን ቁፋሮ ቦታ ላይ በደረሰ የመሬት መንሸራተት የሟቾች ቁጥር ከ200 በላይ መድረሱን የአገሪቱ መንግሥት አስታውቋል።

በታጣቂዎች ቁጥጥር ስር በሚገኘው የሀገሪቱ ትልቁ የኮልታን ማዕድን ቁፋሮ ቦታ ላይ ማክሰኞ ዕለት የማዕድን ማውጫ ጉድጓድ መደርመሱን የዓይን እማኞች ለኤኤፍፒ የዜና ወኪል የገለጹ ሲሆን፤ መጀመሪያ ላይ ስድስት ሰዎች መሞታቸው ተነግሮ ነበር።

የሩባያ የማዕድን ቁፋሮ ቦታ ከሰሜን ኪቩ ግዛት ዋና ከተማ ጎማ በስተምዕራብ 70 ኪሎ ሜትር ገደማ ርቀት ላይ የሚገኝ ሲሆን፤አካባቢው በሩዋንዳ ይደገፋል በሚባለው ኤም 23 የታጠቀ ቡድን ቁጥጥር ስር ነው።

የሀገሪቱ የማዕድን ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ፤ በጊዜያዊ መረጃው መሠረት 70 ሕፃናትን ጨምሮ ከ200 በላይ ዜጎች ሕይወታቸውን ያጡ ሲሆን፤ በርካቶች ደግሞ ቆስለዋል ብሏል።

ኤኤፍፒ የሟቾቹን ቁጥር በገለልተኛ አካል ማረጋገጥ አለመቻሉን አንስቶ፤ ይህም የሆነው አካባቢው ራቅ ያለ በመሆኑ፣ የሰብዓዊ ድርጅቶችም ሆኑ ዋና ዋና የጤና ተቋማት ተደራሽነት የሌላቸው በመሆኑና የቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎትም በተደጋጋሚ የሚቋረጥበት በመሆኑ ነው ሲል አስታዉቋል።

እስከዳር ግርማ

የካቲት 26/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *