ቻይና አደገኛውን የኤሌክትሪክ ጥገና በቴክኖሎጂ ተካች

በቻይና ሁቤይ ግዛት አንድ ዘመናዊ ሮቦት በ10 ኪሎ ቮልት ከፍተኛ የኃይል መስመር ላይ አስቸጋሪ ጥገናዎችን በተሳካ ሁኔታ በማከናወን የሰውን ጉልበት ተክቷል።

ብዙዎች እንደ ኤሌክትሪክ እና ብየዳ ያሉ ሙያዎች ከቴክኖሎጂ ወረራ ነፃ እንደሆኑ ቢያስቡም፣ ይህ ግስጋሴ ግን ማንም ከለውጡ እንደማያመልጥ አመላካች ሆኗል።

ይህ ሮቦት የሌዘር መቁረጫን በመጠቀም የሽቦ ሽፋኖችን በጥንቃቄ መላጥና ግንኙነቶችን ያለምንም ስህተት ማጥበቅ ይችላል ተብሏል፡፡

ቀደም ሲል የኤሌክትሪክ ባለሙያዎች አገልግሎት እንዳይቋረጥ ሲሉ ሕይወታቸውን ለአደጋ አጋልጠው በከፍተኛ ቮልቴጅ መስመሮች ላይ ይሠሩ ነበር። አሁን ግን ይህ ሮቦት የሰውን ሕይወት ለአደጋ የሚያጋልጡና በየዓመቱ የሺዎችን ሕልውና የሚቀጥፉ አደገኛ ተግባራትን በመረከብ የሥራ ደህንነትን አስተማማኝ ማድረጉ ነው የተገለፀው፡፡

ቴክኖሎጂን ሥራ እንደሚቀማ ከመመልከት ይልቅ፣ የሰውን ልጅ ከሞት አደጋ የሚታደግ ወሳኝ ረዳት አድርጎ መውሰዱ ይሻላል መባሉን ኦዲቲ ሴንትራል ዘግቧል፡፡

ሐመረ ፍሬው

የካቲት 27/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *