ከ8መቶ70 በላይ በሚሆኑ የምግብና ጤና ተቋማት ላይ እርምጃ ተወሰደ

የአዲስ አበባ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን በባለፉት ሰባት ወራት ባከናወነው የቁጥጥር ስራ፤የህብረተሰቡን ጤና አደጋ ላይ በሚጥሉ 8መቶ75 ተቋማት ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ መውሰዱን አስታውቋል።

የባለስልጣኑ የምግብና ጤና ነክ ተቋማት ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ እስጢፋኖስ ጌታቸው እንደገለጹት፤ በማዕከልና በ11ዱም ቅርንጫፎች በተካሄደው በዚህ ኦፕሬሽን 7መቶ33 ተቋማት የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው ሲሆን፤ 1መቶ19 ተቋማት ላይ ደግሞ ጊዜያዊ እሸጋ ተደርጓል።

በተጨማሪም ከተሰጣቸው ፈቃድ ውጭ ሲሰሩ የተገኙ 3 ተቋማት ፈቃዳቸው እንዲሰረዝ ሲደረግ፤ 20 ተቋማት ደግሞ በገንዘብ መቀጣታቸውን ተናግረዋል።

በዚሁ የቁጥጥር ወቅት ጥራት የሌላቸውና ለጤና አስጊ የሆኑ ግምታዊ ዋጋቸው ከ52.6 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጡ የምግብና ጤና ነክ ምርቶች እንዲሁም የትምባሆ ህግን ተላልፈው የተገኙ ምርቶች እንዲወገዱ መደረጉን አንስተዋል።

ባለስልጣኑ ክፍተት የታየባቸው ተቋማት ስታንዳርዱን ጠብቀው እንዲሰሩ የክትትልና የድጋፍ ስራውን አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ዳይሬክተሩ ገልፀዋል።

ሐመረ ፍሬው

የካቲት 30/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *