በቱርክ በኤርዶጋን ተቀናቃኝ እና በሌሎች 400 ሰዎች ላይ የሙስና ችሎት ተጀመረ

የኢስታንቡል ከንቲባ ኤክሬም ኢማሞግሉ ከ400 በላይ ከሚሆኑ ሌሎች ተከሳሾች ጋር ፍርድ ቤት ቀርበዋል።

ተከሳሾቹ በሰፊ የሙስና ወንጀል የተከሰሱ ሲሆን፤ተቺዎች ግን ጉዳዩ በቱርክ ተቃዋሚዎች ላይ ያነጣጠረ ፖለቲካዊ እርምጃ ነው ይላሉ።

ለአንድ ዓመት ገደማ በእስር ላይ የሚገኙት ኢማሞግሉ፤ ለ23 ዓመታት ስልጣን ላይ የቆዩት የፕሬዝዳንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን ዋነኛ ተቀናቃኝ ናቸው።

እርሳቸው በቁጥጥር ስር በዋሉ በጥቂት ቀናት ውስጥ፤ በ2028 ለሚካሄደው ምርጫ የዋነኛው ተቃዋሚ ፓርቲ እጩ ሆነው ተመርጠው ነበር።

የችሎቱ ሂደት በውጥረት ውስጥ የጀመረ ሲሆን፤ ኢማሞግሉ የመናገር ዕድል እንዲሰጣቸው ቢጠይቁም የዳኞች ቡድኑ ጥያቄያቸውን ውድቅ ማድረጉን የሃልክ ቲቪ የዜና ጣቢያ እና ሌሎች መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።

ከ402ቱ ተከሳሾች መካከል አብዛኞቹ፣ ኢማሞግሉ ከ2019 ጀምሮ በሚመሩት የኢስታንቡል ሜትሮፖሊታን ማዘጋጃ ቤት ውስጥ የሚሰሩ ናቸው።

ብዙዎቹ የሪፐብሊካን ሕዝባዊ ፓርቲ የተመረጡ ባለስልጣናት ሲሆኑ፤ጋዜጠኞችም ከተከሳሾቹ መካከል ይገኙበታል።

ባለፈው ዓመት መጋቢት የኢማሞግሉ መታሰር፤ ላለፉት አሥር ዓመታት በቱርክ ያልታየ የጎዳና ላይ ተቃውሞዎች መካከል ትልቁን ለሳምንታት የቀጠለ ተቃውሞ ቀስቅሶ ነበር።

ኢማሞግሉ ጥፋተኛ ሆነው ከተገኙ፤ በአጠቃላይ ከ2 ሺህ ዓመታት በላይ የሚዘልቅ የእስር ቅጣት ሊጣልባቸው ይችላል።

እስከዳር ግርማ

መጋቢት 01/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *