ፈረንሳይ ወደ መካከለኛው ምስራቅ የጦር መርከቦቿን ልታሰማራ መሆኑን አስታወቀች

የፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ሀገራቸው በመካከለኛው ምስራቅ ያለውን ውጥረት ተከትሎ የባህር ኃይል ስምሪት እንደምታደርግ አስታዉቀዋል።

ፕሬዝዳንቱ እንደገለጹት፤ ፈረንሳይ አንድ የአውሮፕላን ተሸካሚ መርከብን ጨምሮ ወደ 12 የሚጠጉ የጦር መርከቦችን ወደ ሜዲትራኒያን እና ቀይ ባሕር ቀጣና ታሰማራለች።

ማክሮን አክለውም፤ በስትራቴጂካዊው የሆርሙዝ የባሕር ወሽመጥ አካባቢ የሚገኙ አጋር ሀገራትን ለመደገፍም አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ የፈረንሳይ የጦር ኃይል ወደ ስፍራው ሊያመራ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥተዋል።

ይህ የፈረንሳይ እርምጃ የተወሰደው በቀጣናው ያለው የጸጥታ ስጋት በጨመረበትና አጋር ሀገራት ድጋፍ በሚሹበት በዚህ ወቅት መሆኑ ተመልክቷል።

ልዑል ወልዴ

መጋቢት 01/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *