በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች እና የጸጥታ ችግሮች የሴት ተማሪዎችን የትምህርት ተሳትፎ እያደናቀፉ ነው ተባለ

የክልሉ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ሃላፊ ወይዘሮ አለምነሽ ይባስ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደገለጹት፤ በክልሉ የሚስተዋሉ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች በተለይም ያለ ዕድሜ ጋብቻ ሴት ተማሪዎች ትምህርታቸውን እንዲያቋርጡ የሚያደርግ ዋነኛው ምክንያት ሆኖ ቀጥሏል።

እንዲሁም ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው በመቅረት ወደ ወርቅ ቁፋሮና መሰል የገቢ ማስገኛ ስራዎች መሰማራታቸው በሴቶች የትምህርት ተሳትፎ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እያሳደረ ይገኛል ብለዋል።

በተጨማሪም በክልሉ የሚስተዋለው የጸጥታ ችግርም በሴቶች እንቅስቃሴና ተጠቃሚነት ላይ የራሱ የሆነ ጫና ማሳደሩ ተመላክቷል።

እነዚህን ችግሮች ለመቅረፍም ቢሮው ከክልሉ ብሄረሰብ ምክር ቤት፣ ከሃይማኖት አባቶች እና ከሀገር ሽማግሌዎች ጋር በቅንጅት እየሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

በተለይም ያለ ዕድሜ ጋብቻን ለመከላከልና በትዳር ምክንያት ትምህርት ያቋረጡ ሴቶችን በድጋሚ ወደ ትምህርት ገበታቸው ለመመለስ ሰፊ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች እየተከናወነ መሆኑን አንስተዋል።

ሐመረ ፍሬው

መጋቢት 07/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *