በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ ከ1 ሺህ 1መቶ በላይ ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል ተባለ፡፡

በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ያሉ 1 ሺህ 1መቶ92 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው መመለሳቸዉ ተሰምቷል፡፡
‎
‎በሳምንቱ ውስጥ በተደረገ 5 ዙር በረራ የተመለሱት 1ሺህ 1መቶ73 ወንዶች እና 16 ሴቶች እንዲሁም 3 ጨቅላ ህፃናት ሲሆኑ፤ ከተመላሾች መካከል 34 ዕድሜያቸው ከአስራ ስምንት አመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ይገኙበታል።
‎
‎መስከረም 5 ቀን 2018 በተጀመረው ዜጎችን ወደ ሀገር ቤት የመመለስ ስራ እስካሁን 59 ሺህ 52 ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገር መመለስ ተችሏል።
‎
‎የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በህገወጥ የሰዎች ዝውውር አስከፊነት ዙሪያ ህብረተሰቡን ለማስገንዘብ፣ መደበኛ ያልሆነ ፍልሰትን ለመከላከልና ደህንነቱ የተጠበቀ የፍልሰት አማራጭን ለማበረታታት የሚያስችሉ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል።
‎
‎በተጨማሪም ለተመላሽ ዜጎች በአየር ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ የማድረግ እና ከቤተሰብ ጋር የማቀላቀል ስራው ከሚመለከታቸው ባለድርሻና አጋር አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ እንደሚገኝ አስታዉቋል።

መጋቢት 07/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *