የዓለም የኃይል አቅርቦት እንዲቀጥል ሰላም ‘ወሳኝ’ መሆኑን የአውሮፓ ህብረት ኃላፊ ገለጹ
በአውስትራሊያ ጉብኝት እያደረጉ ያሉት የአውሮፓ ህብረት ፕሬዝዳንት ኡርሱላ ቮን ደር ሌየን፣ በኢራን ያለውን ጦርነት ለማቆም በንግግር የሚገኝ ሰላም እንደሚያስፈልግ አሳሰበዋል።አሁንም ተጠናክሩ በቀጠለው ግጭት “በጣም ማዘናቸውንም” ገልጸዋል።
ቮን ደር ሌየን በካንቤራ ከአውስትራሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር አንቶኒ አልባኒዝ ጋር በጋራ በሰጡት መግለጫ፣ “በመካከለኛው ምስራቅ የምናየውን ግጭት የሚያቆም ፤ በድርድር ላይ የተመሰረተ መፍትሄ ማምጣት እጅግ አስፈላጊ ነው” ብለዋል።
ጦርነቱ ሲያበቃ አንዳንድ የአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት የሆርሙዝ ሰርጥን ለመጠበቅ በሚደረገው “ተልዕኮ” ውስጥ ለመሳተፍ እየተዘጋጁ መሆኑን ቮን ደር ሌየን ገልጸዋል።
አክለውም “ሁላችንም በጋዝ እና በነዳጅ ዋጋ፣ በንግድ ድርጅቶቻችን እና በማህበረሰባችን ላይ የሚፈጠረውን ተጽዕኖ እንረዳለን” ካሉ በኋላ የንግድ መስመሩ “ለዓለም አቀፍ የኃይል አቅርቦት መስመሮች ወሳኝ” መሆኑንም ጠቁመዋል ሲል የዘገበው ቢቢሲ ነው።
መጋቢት 15/2018 ዓ.ም
