ኢራን የቀድሞ የአብዮታዊ ዘብ አዛዥን የብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤት አዲስ ዋና ጸሐፊ አድርጋ ሾመች

ኢራን በአየር ድብደባ የተገደሉትን አሊ ላሪጃኒን በመተካት፤ የቀድሞ የአብዮታዊ ዘብ አዛዥን የሀገሪቱ የብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤት አዲስ ዋና ጸሐፊ አድርጋ ሾማለች።

የኢራን መንግሥት ቴሌቪዥን አዲሱን ዋና ጸሐፊ መሐመድ ባገር ዞልቃድር ናቸዉ ብሏል፡፡

ሹመቱ በኢራኑ ፕሬዝዳንት መሱድ ፔዜሽኪያን ምክትል ይፋ የተደረገ ሲሆን፤ በሀገሪቱ ጠቅላይ መሪም ጸድቋል።

ላሪጃኒ መጋቢት 17 በታለመ የአየር ጥቃት የተገደሉ ሲሆን፤ ይህም አሁን ለቀጠለው ግጭት ከፍተኛ መባባስ እንደ ምክንያት ተወስዷል።

መሐመድ ባገር ዞልቃድር በእስላማዊ አብዮታዊ ዘብ ውስጥ የብርጋዴር ጄኔራልነት ማዕረግ ያላቸው ሲሆን፤ቀደም ሲል ለደህንነት ጉዳዮች የሀገር ውስጥ ጉዳይ ምክትል ሚኒስትርነትን ጨምሮ በከፍተኛ የደህንነት የሥራ መደቦች ላይ አገልግለዋል።

ይህ ሹመት የተሰጠው ከእስራኤል ጋር በቀጠለው ግጭት በኢራን ውስጥ ተከታታይነት ያላቸው የከፍተኛ አመራሮች ሞት ካጋጠመ በኋላ ነው።

እስከዳር ግርማ

መጋቢት 15/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *