በሪል ስቴት ዘርፍ አልሚዎች እና ተጠቃሚዎች መሀከል አስተማማኝ በሆነ መንገድ ግብይቶች እንዲፈፀሙ የተዘጋጁ ሥርዓቶችን ለማስተዋወቅ ያለመ መድረክ መዘጋጀቱ ተነገረ

“ኢትዮ ሆም- ኤክስፖ 2026” በሚል የሪልስቴት ኤክስፖ በለንደን ከተማ የሚካሄድ እንደሆነም ተገልጿል።

በለንደን የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ከኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎት እና ኤድማር ቬንቸርስ ከተባለ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ተቋም ጋር በመተባበር ያዘጋጀዉ ነዉ ተብሏል።

በዩናይትድ ኪንግደም የሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያንን የመኖሪያ ቤት ፍላጎት ለማሟላት ይረዳል በተባለ ኤክስፖ፤ የፓናል ውይይት በዘርፉ ያለውን የመረጃ ክፍተት እንዲሁም አዳዲስ የወጡ ፖሊሲዎች ተፈፃሚነት ላይ ውይይት እንደሚደረግ ተነግሯል።

ኤክስፖው ከግንቦት 15 – 17 ቀን 2018 ዓ.ም ለሶስት ቀናት በለንደን ከተማ የሚካሄድ ሲሆን፤ የአዲስ አበባን ንግድ ምክር ቤት በኤክስፖው የሚሳተፉ የሪል ስቴት አልሚዎች በታቀደለት ግዜ፣ ጥራት እና ዋጋ ለደንበኞቻቸው ቃል የገቡትን ቤት ማስረከብ የሚችሉ መሆናቸውን እና የሚያቀርቧቸውን ሰነዶች ህጋዊነት በተቀመጡ መመዘኛዎች የማጣራት ሂደት የሚያልፉ ይሆናል ተብሏል።

የዳያስፖራ ማኅበረሰብ አባላት ተሣትፎ በማድረግ አገልግሎት እንዲያገኙ፤ ሪል ስቴት አልሚ ድርጅቶች፣ባንኮች፣ የፋይናንስ ተቋማትም በዚህ ኤክስፖ ምርትና አገልግሎታቸውን እንዲያስተዋውቁ ጥሪ ቀርቧል።

ቁምነገር አየለ

መጋቢት 21/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *